ኢህአዴግ ራሱን አደነቀ- ግምገማ ተቀምጧል

የኢህአዴግ ም/ቤት ስምንተኛ ድርጅታዊ ስበሰባውን ከትናንት ጀምሮ እያካሄደ ሲሆን የድርጅቱን እቅንስቃሴና አቅጣጫ እየገመገመ መሆኑ ታውቋል። በወያኔ ሓርነት ትግራይ ሊቀመንበር በአቶ መለስ ዜናዊ ሊቀመንበርነት የሚመራው የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ሪፖርት ማቅረቡም ተነግሯል። በሪፖርቱም መሠረት ነገሮች ሁሉ በተቀመጠላቸው አቅጣጫ እየተጓዙ መሆናቸው ተገልጿል። ለወደፊቱም በየደረጃው የሚገኙ መንግሥታዊና ድርጅታዊ አስፈጻሚ አካላት ትኩረት ሰጥተው እንዲቀሳቀሱባቸው የሚያስፈልጉ አቅጣጫዎች እየተነደፉ መሆኑም ተነግሯል። ባለፈው […]

ሕወሓት በቴሌኮሙኒከሽንና ፖስታ ድርጅትም ተከበረ

አዲስ አበባ የቴሌኮሙኒኬሽንና የፖስታ ድርጅት የሚገኙ 700 የወያኔ ሓርነት ትግራይ አባላትና ደጋፊዎች የድርጅታቸውን 34ኛ የልደት በዓል ማክበራቸው ተዘግቧል። የካቲት 22/2001 በተካሄደው በዚሁ በዓል ላይ የደህንነት ከፍተኛ ባለሥልጣና የነበሩትና የወያኔ ሓርነት ትግራይ ማእከላዊ ኮሚቴ አባልና የቴሊኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ደብረ ጽዮን ገ/ሚካኤል በእንግድነት መገኘታቸው ተዘግቧል። “መንግስታዊው ቴሌኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን እያለ ሌላ ተደራቢ ተቋም ማቋቋም ለምን ያስፈልጋል?” […]

የገንዘብ ሚኒስትራችን እድሜ ስንት ነው?

ሰሞኑን መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ የገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር በውጭ ምንዛሬ እጥረት የተነሳ መንግሥት ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ነው ማለታቸው ተዘግቧል። ካለፈው ዓመት ጀምሮ በተፈጠረው የዓለም የፋይናንስ ቀውስ ምክንያት የነዳጅ የሸቀጦችና የኮንስትራክሽን እቃዎች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩንም ገልጸዋል። በውጭ ምንዛሪ የሚጠቀሙ ነጋዴዎችም ሆኑ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት በመመካከር፣ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ጥራት በመጨመርና በብዛት በመላክ፣ የውጭ ምንዛሪ […]

በአዲሱ አዋጅ ያልተመዘገቡ ጋዜጦች ይሰረዛሉ

የመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ነጻነትን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ መሰረት ያልተመዘገቡ ጋዜጦችና መጽሔቶች ከአምስት ቀናት በኋላ ይሰረዛሉ ተባለ። ከ57 ጋዜጣና መጽሔቶች እስካሁን ቀርበው ፎርም የሞሉት 22 ሲሆኑ ሰርትፊኬት የተሰጣቸው ሰባት ብቻ ናቸው።የኢትዮጵያ ብሮድ ካስት ባለሥልጣን ዳይሬክተር አቶ ደስታ አስፋው እንደገለጹት የመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ነጻነትን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ መሰረት አዋጁ ከመውጣቱ በፊት የተቋቋመ ማንኛውም ፕሬስ አዋጁ ከፀናበት ህዳር […]

ወንድ እፈልጋለሁ – የእንቁጣጣሽ ስልክ ከዲሲ

የእንቁጣጣሽ ስልክ ከዲሲ

መንግሥት 4.9 ሚሊዮን ህዝብ ተርቧል አለ

በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው የምግብ እጥረት 4 ነጥብ 9 ሚሊዮን የሚደርሱ ዜጎች የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ። የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ምትኩ ካሳ ዛሬ ለአገር ውስጥና ለውጪ አገር ጋዜጠኞች እንደገለጹት መንግሥት ከለጋሽ አገሮችና ድርጅቶች ጋር ባደረገው የመስክ ጥናት ለችግሩ የተጋለጡ ዜጎች ብዛት 591 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምግብ ያስፈልጋቸዋል። የምግብ እጥረቱ […]

ከመንጋው ፈቀቅ በል!

ጊዜው አጭር ነው። አምባገነኖች አይሻሻሉም፣ ጠማሞች አይሰተካከሉም። ደናቁርት አይጠበቡም። ስግብግቦች አይጠግቡም፣ ሌቦች አይታቀቡም፣ ፖለቲከኞቻችን አንድ አይሆኑም..ነጻ ወጪዎቹ ጎሰኞች ነጻ ወጥተው አያበቁም! ተገዢም ሆነው ገዢም ሆነው አየናቸው። የበታችነትና የጥላቻ ስሜትን ከደማቸው ውስጥ ለማጠብ የህይወት ዘመናችን አይበቃም። በዚያ ላይ በዚህች አጭር እድሜ በአጭሩ የሚቀጭ ችግር የለንም። ለውጥ ገና ናት። ተወደደም ተጠላም እውነቱ ይህን ይመስላል። ተስፋ ለማድረግ ተስፋ […]

አባማቶጵያ!

ኦባማ ከምንም ነገር በፊት አንደበታቸው ይጣፍጣል። ስለሆነም በወጣቱ ብቻ ሳይሆን በሁሉ ሰው ጆሮ ፖለቲካን በቀላሉ ሊያንቆረቁሩ ችለዋል። ንግግራቸው እንደኛ አገር የቸከ የመነቸከ ከዓመት ዓመት የማይለወጥ አይደለም። የኛ ንግግር አብዮት- ጎሳ -ብሄር ብሄረሰብ- ነፍጠኞች- ፀረ ህዝቦች… በሚሉት ገፍታሪ ቃላት የተሞላ ይመስላል። እውነት ነው አሜሪካና ኢትዮጵያ ይለያያሉ። አሜሪካውያን ያን ያህል የሰነበተ ሥር የሰደደ ችግር የላቸውም። ከተቸገሩበት የታደሉት […]

ህግ እና ኮሙዪኒቲያችን

በቸልተኝነት የሚደርስ የመኪና አደጋና ሕግ ከቸልተኝነት ጋር ተያይዞ በግለሰብ ላይ የሚደርስ ጉዳት በተለያየ ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። የመጀመሪያው ጥፋቱን ያጠፋው አካል በግዴለሽነት የተነሳ ቀጥተኛ የሆነን አደጋ ሰውና ንብረት ላይ ሲያደርስ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ኃላፊነትን ካለመወጣት ጋር ተያይዞ ላይፈጠር ይችል የነበረን አደጋ ሳይከላከላል ሲቀር ነው። ከቸልተኝነት ጋር ተያይዘው ከሚጠቀሱ አደጋዎች መካከል ተንሸራቶ መውድቅ፣ የአዛውንቶች ማረፊያ ውስጥ የሚደርስ […]

የቤተመንግሥቱ ጄነራል-ፍሬሰንበት

የንጉሠ ነገሥቱን ዙፋን ፣ጃንሆይ ትተውት እንደሄዱት ተነጥፎ የሚገኘው አልጋና መኝታ ቤታቸው ይህን ይመስላል። የወግ አልባሳትና ጫማዎቻቸው፣ ከነመላው የቤተመንግሥቱ ቅርሶችና ታሪኮች ጋር ዛሬም ድረስ ተጠብቀው ይገኛሉ ። ይህን ቅርስ በአደራ ጠብቀውና ተከላክለው ያቆዩት ብ/ር ጄነራል ፍሬሰንበት አምዴ ነበሩ። በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ላለፉት 30 ዓመታት ቤተመንግሥትን በዋናነት ሲያስተዳድሩ ከነበሩት ጄነራል ፍሬሰንበት ህይወት ጋር አብሮ የሚጻፍ […]

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios