50 ጥያቄዎች ለዶ/ር ብርሃኑ ነጋ
ለሰው ሲያሳይ አየሁትና “እስኪ እሱን ፎቶግራፍ ወዲህ አምጣው?” አልኩት። ከላይ የምታዩትን ሰጠኝ። ግፋ ቢል የአስር ወይ አስራ አንድ ዓመት ልጅ ቢሆን ነው። 6ኛ ክፍል ግድም እያለ ተማሪ ቤት የተነሳው ፎቶ መሆኑ ነው። ደብረዘይት ነው የተወለደው። በአዲስ አባባው ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ንቃንቄ ተሳታፊ የሆነው ገና የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ እንደሆነ ነው። የመንግሥት ለውጥ ሆኖ ደርግ ሥልጣን ላይ ሲወጣ ወደ አሲምባ ከወጡ የኢህአፓ ወጣቶች አንዱ ነበር። “ምናልባት የ16 እና የ17 ዓመት ልጅ ነበርኩ” ብሎናል። ከዚያ በሱዳን አድርጎ ወደ አሜሪካን አገር ለስደት መጣ ።አሜሪካም ኒዮርክ ሆኖ  ስብበሳባና የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ምሁራንና ሌሎች ዜጎችን በማሳተፍ ሲያስተባብር ቆየ። በየዩኒቨርሰቲው ዶክተር እስኪሆን ተምሮ አስተምሮ ሲያበቃ ለውጥ የመጣ ሲመስለው ወደ አገሩ ገባ። ፖለቲካ ውስጥ ለመግባት ሳይሆን ለምርምር ሥራና ለማስተማር ነበር። እንደ “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማህበር” የመሳሰሉትን በማቋቋምና የምርምር ሥራዎችን ሲሰራ ከፖለቲካ ዓለም ትንሽ ተለይቶ ቆየ። ዳር ሆኖ ከማየት ወደፖለቲካው ዓለም በመግባት ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብሎ በማመኑ በምርጫው አካባቢ ተመልሶ ወደ ፖለቲካው ዓለም ገባ። የአሁኑ ፖለቲካ ግን እንደልጅነቱ ጊዜ አይደለም። ሰዎችና ድርጅቶች በየጎሳቸው ተበትነው በአንድ ብሄራዊ ጥላ ሥር አልተቀናጁም። ከመሰሎቹ ጋር ቅንጅት ሆኖ ብትንትኑን ፖለቲካ  ለማቀናጀት ተነሳ። ከህዝብ ድጋፍ ጋር ከጓደኞቹ ጋር የጀመሩት ቅንጅት ፍሬ አፍርቶ ግንቦት 7/2005 ዓም ታሪክ ተሠራ። እሱም ለአዲስ አበባ ከንቲባነት ታጨ። ግን አልሆነም ሁሉም ነገር በአጭር ተቀጨ። ጨዋታው ፈረሰ- ዳቦ ተቆረሰ። መሪዎች ታሠሩ። ሰዎች ተገደሉ። ቅንጅትን ለማፍረስ ብሄራዊ መግባባት የተደረሰ ይመስል ፣ ቅንጅቶች ራሳቸው ከኢህአዴግ  ጋር ተባብረውና ተጠዳድፈው ቅንጅትን አፈረሱት። እንደገና ጨለመ። ግንቦት 7/2005 ሌሊቱን የተጠበቀው ብርሃን ሳይነጋ ቀረ። ከእንግዲህ ይነጋ ይሆን? (ለማንበብ)

1 Comment for “”

  1. Your blog is great你的部落格真好!!
    If you like, come back and visit mine: http://b2322858.blogspot.com/

    Thank you!!Wang Han Pin(王翰彬)
    From Taichung,Taiwan(台灣)

Leave a Reply to superstar racing

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios