አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ ም/ል ሆነ ተመረጡ

የኢህአዴግ ምክር ቤት አርብና  ቅዳሜ  ባደረገው መደበኛ  ሰብሰባው የግንባሩን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር መረጠ ።
ምክር ቤቱ   አቶ  ሀይለማሪያም ደሳለኝን  የግንባሩ ሊቀመንበር አድርጎ  የመረጠ  ሲሆን ፥  አቶ  ደመቀ መኮንንን  ደግሞ በምክትል ሊቀመንበርነት መርጧል ።
መግለጫ  ቅዳሜ ከሰዓት  በኋላ  በተደረገው  የአመራር  ምርጫ  አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ከቀረቡት ሶሰት እጩዎች  መካከል ሙሉ  ድምፅ  በማግኘት ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል ።
በመግለጫው ላይ እንደተመለከተውም የአመራር  ምርጫው ከመካሄዱ በፊት  የኢህአዴግ ምክር ቤት አባላት ቀደም ሲል ፓርቲው ባስቀመጠው የመተካካት እቅድ መሰረት ምርጫው እንዲካሄድ  ተስማምተዋል ።

Leave a Reply

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios