የኢትዮጵያ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን በሱዳን 5 ለ 3 ተሸነፈ         

ከትንናት በስቲያ ካርቱም ላይ ከሱዳን የተጫወተው  የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን 5 ለ3  ተሸንፏል ። በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት እየተመራ የቆየው የኢትዮጵያ ቡድን ከእረፍት መልስ ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር ሶስት አቻ ሆኖ ነበር ።ይሁን እንጂ ጨዋታው ሊጠናቀቅ አካባቢ የሱዳን ብሄራዊ ቡድን ባገኛቸው ሁለት ፍጹም ቅጣት ምቶች ሁለት ተጨማሪ ጎሎችን ለማግኘት ችሏል ።
የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ አዲስ አበባ ላይ ያደረጋል ። ኢትዮጵያ በሁለት ጎል ልዩነት ማሸነፍ ከቻለች ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የማለፍ እድል ይኖራታል።

Leave a Reply

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios