ለወ/ሮ አዜብ መስፍን 6 ኩባንያዎች ተጨመሩላቸው

ደጀናና እና ኤፈርት ተዋሃዱ
በወያኔ ሓርነት ትግራይ ሥር የሚገኘውና 6 ትላልቅ ኩባንያዎችን የሚያስተዳድረው ደጀና የተባለው ግዙፍ የንግድ ኩባንያዎች ጥምረት ኤፈርት ከተባላው ሌላኛው የወያኔ ሓርነት ትግራይ ኩባንያ ጋር ከኤፕሪል 1/2009 ጀምሮ የተዋሃደ መሆኑ ተዘግቧል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ መለስ ውሳኔ የተላለፈው የውህደት ውሳኔ የባለቤታቸው የወ/ሮ አዜብ መስፍንን ሹመት ተከትሎ የመጣ መሆኑም ተነግሯል። ወ/ሮ አዜብ በአቶ ስብሐት ነጋ ምትክ የኤፈርት ኃላፊ ሆነው በአቶ መለስ ዜናዊ የተሾሙት በቅርቡ መሆኑ ይታወሳል። በመሆኑም 6 ኩባንያዎችን (Biruhe Tessfa plastic factory, Machew Particles Board, Dimma Honey processing factory, Alagye Forestery, National Geo-Textile Factory and Aberdelie Cattle Fattening and exporter.) ያቀፈውን ደጀናን በቦርድ ም/ሊቀመንበርነት የሚያስተዳድሩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ይሆናሉ ማለት ነው። እንደካፒታል ዘገባ ደግሞ ቀደም ሲል የኤፈርት መሪዎች የነበሩት 7ቱ የወያኔ ሓርነት ትግራይ ፓርቲ ሲኒየር ባለሥልጣናት፣ ስዬ አብርሃ፣ ስዩም መስፍን፣ አቦይ ስብሐት ነጋ የመሳሰሉት እንደነበሩ ተሰምቷል። ኤፈርት 13 ግዙፍ ኩባንያዎችን – (Addis Pharmaceutical Factory (APF), Almeda Textiles Factory, Express Transit Service Plc (EXTRAN), Ezana Mining Development (EMD), Guna Trading House, Hiwot Agricultural Mechanization, Mesfin Industrial Engineering, Messebo Cement Factory; are some of the companies under the control of EFFORT.) በሥሩ ያቀፈ መሆኑ ሲገለጽ አሁን 6 ተጨማሪ ኩባንያዎችን በሥሩ ለማስተዳደር ይረዳዋል። የደጀናም ሆኑ የኤፈርት ዓላማዎች በጦርነት ተጎድታለች የተባለችውን ትግራይ ክልል ብቻ ማቋቋምና መገንባት ነው።

ለተጨማሪ ንባብ
MEGA FUNDS MERGE

Leave a Reply

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios