የነገው የፓርላማው ስብሰባ ላልተወሰነ ጊዜ ተላለፈ

መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝን የጠቅላይ ሚንስትርነት ሹመት ለማጽደቅ አስቸኳይ የጠራውን ስብሰባ ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፉን በኮሙዪኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በኩል አስታውቋል።

Clinton, Ki-moon, Susan Rice Send Condole With Ethiopia Over PM’s Death

ፓርላማው ነገ ይሰበሰባል -ኃ/ማርያም ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ሐሙስ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው ።
ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ ላይ እንደተመለከተው አስቸኳይ  ስብሰባው የሚካሄደው ነገ ኦገስት 23 ከማለዳው 2 ሰዓት ከ30 ጀምሮ ነው ።

ስብሰባው በተለያዩ  የመገናኛ ብዙሃንም የቀጥታ  ስርጭት  እንደሚያገኝ ተመልክቷል ።
በዚህ አስቾካይ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ቃለ መሃላ ይፈፅማሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከጋዜጠኞች ጋር በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት  አቶ መለስ ከህመማቸው በማገገም ላይ በነበሩበት ወቅት በቅርበት እየተደዋወሉ  በስራ ጉዳዮች ላይ ሲመክሩ እንደነበር ገልጸዋል።

በእለቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤትና  የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ  በተለያየ  ሰዓት ውይይት ማድረጋቸውን ያነሱት አቶ ሀይለማሪያም  ፥ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ  አባላት የአገሪቱን የአድገትና ትራንስፎርሜሽን  እቅድ  ለማስፈፀም ቃል ኪዳናቸውን አድሰዋል ብለዋል ።

በህገመንግሥቱ መሠረት ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው የተመረጡት አቶ ኃይለ ማርያም ፓርላማው መደበኛ ስራውን ሲጀመር ገዢው ፓርቲ  ያመነበትና ብቁ  እጩ አቅርቦ በም/ጠቅላይ ምኒስትርነት የሳቸውን ቦታ የሚተካ ሰው እንደሚመርጥም ገልጸዋል።

Leave a Reply

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios