የዲሲ ሜትሮ
የWashington ከተማ ክልል ትራንዚት ባለሥልጣን (Metro)
ሥራ አስኪያጁ የቀረበ የFY2010 የበጀት ረቂቅ
ዓላማ
ይህ ማስታወቂያ የተሰጠው በWashington ከተማ ክልል ትራንዚት ባለሥልጣን (Metro)፣ በWashington የከተማ ዳርቻ ትራንዚት ኮሚሽን፣ በሰሜናዊ Virginia የመጓጓዣ ኮሚሽን እንዲሁም በColumbia ዲስትሪክት በዋና ሥራ አስኪያጁ የቀረበውን የFY2010 የበጀት ረቂቅ እና የአገልግሎት ማስተካከያዎችን ሃሳብ በተመለከተ ውይይት የሚካሄድባቸው ስድስት ህዝባዊ ችሎቶች ሰኔ 28 ቀን 2009 እና በዚያው ሰሞን በሚከተለው መሰረት የጸኑ እንዲሆኑ ፕሮግራም የተያዘላቸው መሆኑን ለመግለጽ ነው፡-
የችሎት ቁጥር 538
ሰኞ ሚያዝያ 13 ቀን 2009
First United Methodist Church
6201 Belcrest Rd
Hyattsville, MD
የችሎት ቁጥር 539
ሰኞ ሚያዝያ 13 ቀን 2009
Marshall Road Elementary School
730 Marshall Rd SW
Vienna, VA
የችሎት ቁጥር 540
ማክሰኞ ሚያዝያ 14 ቀን 2009
First Baptist Church of Wheaton
10914 Georgia Ave
Wheaton, MD
የችሎት ቁጥር 541
ረቡዕ ሚያዝያ 15 ቀን 2009
Arlington County Government
#1 Courthouse Plaza
2100 Clarendon Blvd, Rm. 307
Arlington, VA
የችሎት ቁጥር 542
ረቡዕ ሚያዝያ 15 ቀን 2009
Saint Francis Xavier Church
2800 Pennsylvania Ave SE
Washington, D.C.
የችሎት ቁጥር 543
አርብ ሚያዝያ 17 ቀን 2009
Metro Headquarters Building
600 Fifth Street, NW
Washington, D.C.
ሁሉም ችሎቶች ከምሽቱ 6:30 ይጀምራሉ
እነዚህ ህዝባዊ ችሎቶች የሚካሄዱባቸው ቦታዎች በተሸከርካሪ ወንበር (ዊልቼር) መግባት የሚቻልባቸው ናቸው፡፡ በህዝባዊ ችሎቱ ላይ ለመካፈል የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚን የመሰለ ልዩ እገዛ ወይም ተጨማሪ አገልግሎት እንዲደረግላቸው የሚፈልጉ ወይም እነዚሁኑ መረጃዎች በሌላ መልክ ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ሜትሮ (Metro) አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ ይችል ዘንድ እስከ ሰኞ ሚያዝያ 6 ቀን ድረስ Ms. Danise Peñaን በስልክ ቁጥር 202-962-2511 ወይም TTY: 202-638-3780 ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ እባክዎ
www.wmata.com የሚለውን ድረ-ገጽ ይመልከቱ
የቀረበው ሃሳብ
የWashington ከተማ ክልል ትራንዚት ባለሥልጣን (Metro) ሐምሌ 1 ቀን 2009 ለሚጀምረው የ2010 የሥራ ዘመን (FY2010) ጉልህ የሆነ የበጀት እጥረት አጋጥሞታል፡፡ የሜትሮባስ (Metrobus)፣ የሜትሮሬይል (Metrorail) እና የሜትሮአክሰስ (MetroAccess) አገልግሎቶች በከፊል የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙት ከተሳፋሪዎች ከሚሰበሰብ ገቢ ሲሆን ቀሪውን የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙት ደግሞ በDistrict of Columbia፣ በState of Maryland እንዲሁም በVirginia የሚገኙ የአካባቢ መስተዳድሮች ከሚያደርጉት የገንዘብ ድጎማ ነው፡፡ ሜትሮ (Metro) ይህንን የበጀት እጥረት ለመቋቋም ብዙ ወጪ ቆጣቢ እርምጃዎችን የወሰደ ከመሆኑም ሌላ የሥራ ማስኬጃ በጀቱን ለመቀነስ በማሰብ የሰራተኛ ቅነሳ አካሂዷል፡፡
ሕዝባዊ ችሎቶቹ ዋና ስራ አስኪያጁ ለFY2010 ያቀረቡትን የበጀት ረቂቅ እንዲሁም በDistrict of Columbia፣ በMaryland የከተማ ዳርቻዎች እና በሰሜን Virginia በሚገኙ የተመረጡ የአውቶቡስ መስመሮች ላይ በተደረገው የአገልግሎት ማሻሻያ ማስተካከያ እንዲሁም በMaryland የአውቶቡስ መስመር J7፣ J9, እና W19 እና በVirginia 26A፣E፣W የተሳፋሪዎች ክፍያ ላይ ብቻ አስተያየት ለማሰባሰብ የታለሙ ናቸው፡፡ የቀረቡትን ሃሳቦች በተመለከተ www.wmata.com ከሚለው ድረ-ገጽ ላይ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
ሜትሮ (Metro) በWMATA Compact አንቀጽ 62 መሰረት በDistrict of Columbia, በMaryland የከተማ ዳርቻ እና በሰሜናዊ Virginia ስድስት ህዝባዊ ችሎቶች ያካሂዳል፡፡ ችሎቶቹን የተመለከቱ መረጃዎችን በአካባቢዎቹ ቤተ መጻሕፍት፣ በሜትሮባሶች (Metrobuses) ላይ፣ በሜትሮሬይል (Metrorail) ባቡሮች ላይ እንዲሁም ኢንተርኔት ላይ በwww.wmata.com ድረ-ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
በሕዝባዊ ችሎቶቹ ላይ ንግግር ለማቅረብ እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል
የቀረበውን የአገልግሎት ማሻሻያ ሃሳብ ወይም በዋና ስራ አስኪያጁ የቀረበውን የFY2010 በጀት ረቂቅ በተመለከተ ያላቸውን አመለካከት ማሰማት የሚፈልጉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በሙሉ አመለካከታቸውን መግለጽ እና ድጋፍ ሰጪ መረጃዎቻቸውንና አማራጭ ሃሳቦችን ማቅረብ የሚችሉበት አጋጣሚ ይሰጣቸዋል፡፡ ማመሳከሪያ ዝርዝር ማዘጋጀት ይቻል ዘንድ በእነዚህ ህዝባዊ ችሎቶች ላይ ሃሳባቸውን መግለጽ የሚፈልጉ ግለሰቦችና የድርጅቶች ወኪሎች ስማቸውን፣ አድራሻቸውን፣ የስልክ ቁጥራቸውንና የሚሳተፉበትን ድርጅት (የሚሳተፉበት ካለ) Washington Metropolitan Area Transit Authority, 600 Fifth Street, NW, Washington, D.C. 20001 ለሚገኘው የጸሃፊው ቢሮ (Office of the Secretary)፣ ንግግራቸውን ማቅረብ በሚፈልጉበት ቀን እስከ ከቀኑ 2 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ በጽሑፍ እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ፡፡ እንደ አማራጭ ንግግር ለመስጠት የሚቀርቡ ጥያቄዎች በፋክስ ቁጥር
ሃሳብን በጽሑፍ እንዴት ማቅረብ እንደሚቻል
በጽሑፍ የቀረቡ መግለጫዎችና መረጃዎች Washington Metropolitan Area Transit Authority, 600 Fifth Street, NW, Washington, D.C. 20001 ለሚገኘው የጸሐፊው ቢሮ (Office of the Secretary) እስከ ሰኞ ሚያዝያ 20 ቀን 2009 ከምሽቱ 5 ሰዓት ድረስ ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ እንደ አማራጭ public-hearing-testimony@wmata.com የሚለውን አድራሻ ተጠቅሞ ኢ-ሜል መላክ ይቻላል፡፡ ጥያቄያችሁን ስታቀርቡ እባካችሁ በዚህ ሰነድ ፊተኛ ገጽ ላይ የተመለከተውን የችሎት እና/ወይም የመዝገብ (Docket) ቁጥር አመልክቱ፡፡
የመስመር መወገድ |
||
የጉዞ መስመር (ሮች) |
የመስመር ስም |
ለውጥ |
District of Columbia |
||
M2 |
Fairfax Village – Naylor Road |
ሁሉም አገልግሎት ይቋረጣል፡፡ ለአንዳንድ ተሳፋሪዎች በጉዞ መስመር F14 አማራጭ አገልግሎት ይኖራል፡፡ |
D5 |
MacArthur Blvd. – Georgetown |
ሁሉም አገልግሎት ይቋረጣል፡፡ ለአንዳንድ ተሳፋሪዎች በጉዞ መስመር D6 አማራጭ አገልግሎት ይኖራል፡፡ |
Maryland |
||
B27 |
Bowie – New Carrollton |
ሁሉም አገልግሎት ይቋረጣል፡፡ ለአንዳንድ ተሳፋሪዎች በጉዞ መስመር B21፣ B22፣ T16፣ T17 አማራጭ አገልግሎት ይኖራል፡፡. |
B29, B31 |
Crofton – New Carrollton |
ሁሉም አገልግሎት ይቋረጣል፡፡ ለአንዳንድ ተሳፋሪዎች በጉዞ መስመር B21፣ B22፣ B24፣ B25፣ C28 አማራጭ አገልግሎት ይኖራል፡፡ |
C7, C9 |
Greenbelt – Glenmont |
ሁሉም አገልግሎት ይቋረጣል፡፡ ለአንዳንድ ተሳፋሪዎች በጉዞ መስመር 83፣ 86፣ 87፣ 89፣ C2፣ C8፣ R2፣ R5፣ R12፣ T17፣ Z8፣ Z9 አማራጭ አገልግሎት ይኖራል፤ Ride On 10፣ አውቶብሱ 11፡፡ |
C12, C14 |
Hillcrest Heights |
ሁሉም አገልግሎት ይቋረጣል፡፡ ለአንዳንድ ተሳፋሪዎች በጉዞ መስመር H11፣ H12፣ P12 አማራጭ አገልግሎት ይኖራል፡፡ |
R3 |
Greenbelt – Fort Totten |
ሁሉም አገልግሎት ይቋረጣል፡፡ ለአንዳንድ ተሳፋሪዎች በጉዞ መስመር 83፣ C2፣ C4፣ C8፣ F4፣ F6፣ F8፣ R1፣ R2፣ R4፣ R5፣ R12፣ T16፣ T17 አማራጭ አገልግሎት ይኖራል፤ አውቶብሱ 11፣ 13፣ 14፣ 15፣ 15X፣ 16፡፡ |
W15 |
Indian Head Highway |
ሁሉም አገልግሎት ይቋረጣል፡፡ ለአንዳንድ ተሳፋሪዎች በጉዞ መስመር A2፣ D12፣ D13፣ D14፣ P12፣ W13 አማራጭ አገልግሎት ይኖራል፡፡ |
Virginia |
||
22B |
Pentagon-Army/Navy Dr.-Shirley Pk. |
ሁሉም አገልግሎት ይቋረጣል – አገልግሎቱ በArlington Transit ይተካል |
24P |
Ballston – Pentagon |
ሁሉም አገልግሎት ይቋረጣል – አገልግሎቱ በArlington Transit ይተካል |
|
|
|
የተወገዱ የጉዞ መስመሮች ወይም የመስመር ክፍሎች |
||
የጉዞ መስመር (ሮች) |
የመስመር ስም |
የሚቀነሱ አገልግሎቶች መግለጫ |
Maryland |
||
C4,C2 |
Greenbelt – Twinbrook |
በWheaton እና Twinbrook Stations መካከል ያለው የC4 አገልግሎት በሙሉ ይቋረጣል፡፡ (C2 የሚያገለግለው ከWheaton Station በስተምዕራብ ለሚቀጥሉ ጉዞዎች ብቻ ነው፡፡) |
C8 |
College Park – White Flint |
በሳምንቱ የስራ ቀናት እንቅስቃሴ በማይበዛባቸው ሰዓታትና የቅዳሜ አገልግሎቶች በሙሉ ይቋረጣሉ፡፡ |
J5 |
Twinbrook – Silver Spring |
እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው ሰዓታት ብቻ በከፊል እንዲተኩ ሲባል የተቋረጡትን የC4 እና የQ2 የጉዞ መስመሮች መቀየር፡፡ የአገልግሎቶች መደጋገም ከ30 ወደ 20 ደቂቃ ማሳደግ፡፡ |
L7 |
Connecticut Avenue – Maryland |
L7ን በማስወገድ የL8ን አገልግሎት መጨመር፡፡ |
NH1 |
National Harbor |
ከ Southern Avenue Station ወደ Branch Avenue Station የጉዞ መስመር መቀየር፡፡ |
P17, P18, P19 |
Oxon Hill – Fort Washington |
የሁሉንም ጉዞዎች መስመር ወደ Southern Avenue Station የጉዞ መስመር መቀየር፡፡ ከኤክስፕረስ ተመን ይልቅ መደበኛውን ተመን ማስከፈል፡፡ |
Q2 |
Veirs Mill Road |
የሰሜን Montgomery College (Rockville Campus) እና የደቡብ Wheaton Stationን ለሁልጊዜ ማስወገድ፡፡ በRockville Station እና በMontgomery College መካከል ያለውን የጉዞ መስመር ለተማሪዎች ጉዞ ስለሚፈለግ ባለበት ማቆየት፡፡ |
W13, W14 |
Bock Road |
ሁሉንም የጉዞ መስመሮች ወደ Southern Avenue Station የጉዞ መስመር መቀየር፡፡ ከኤክስፕረስ ተመን ይልቅ መደበኛውን ተመን ማስከፈል፡፡ |
Z2 |
Colesville – Ashton |
በሳምንቱ ቀናት የሚሰጠውን የእኩለ ቀን አገልግሎት ማስወገድ፡፡ ቅዳሜ፡ በWhite Oak እና በColesville መካከል ያለውን አገልግሎት ማስወገድ፡፡ |
Virginia |
||
10A |
Hunting Towers – Pentagon |
በሳምንቱ ቀናት ከምሽቱ 9 ሰዓት በኋላና የቅዳሜና እሁድ አገልግሎቶች በሙሉ ማቋረጥ፡፡ በAlexandria አቅጣጫ የሚሰጠውን የቅዳሜና እሁድ፣ የቅዳሜ ምሽት እንዲሁም የእሁድ Sunday 10A አገልግሎት ለመተካት የ10B አገልግሎትን ማሳደግ፡፡ |
21A,B,C,D,F |
Landmark – Pentagon |
በReynolds St., Edsall Rd., Whiting St., Stevenson Ave., Yoakum Pkwy., Edsall Rd., Van Dorn St., Duke St., I-395 እስከ Pentagon ያለውን በአንድ መስመር መጠቅለል፡፡ |
26A,E,W |
GEORGE (Falls Church service) |
ሁሉንም አገልግሎቶች ማስወገድ ወይም የክፍያ ተመኑን ከ$0.50 ወደ መደበኛው ተመን ($1.35 በጥሬ ገንዘብ/$1.25 SmarTrip)፡፡ |
|
|
|
በተወሰኑ መስመሮች ላይ የክፍያ ተመን መጨመር |
||
የጉዞ መስመር(ሮች) |
የመስመር ስም |
የተመን ለውጥ |
Maryland |
||
J7, J9 |
I-270 Express |
ከመደበኛው ተመን ይልቅ $3.10 በጥሬ ገንዘብ/$3.00 SmarTrip ኤክስፕረስ ተመን ማስከፈል፡፡ |
W19 |
Indian Head Express |
ከመደበኛው ተመን ይልቅ $3.10 በጥሬ ገንዘብ/$3.00 SmarTrip ኤክስፕረስ ተመን ማስከፈል፡፡ |
Virginia |
||
26A,E,W |
GEORGE (Falls Church service) |
ከ$0.50 ወደ መደበኛ ተመን ($1.35 በጥሬ ገንዘብ/$1.25 SmarTrip) ማሳደግ፡፡ |
|
|
|
በአገልግሎት ድግግሞሽ ረገድ የተደረገ ለውጥ |
||
የጉዞ መስመር(ሮች) |
የመስመር ስም |
ለውጥ |
District of Columbia |
||
52, 53, 54 |
14th Street |
እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው ሰዓታት በየአውቶብሶቹ መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት ከ4.5 ወደ 5 ደቂቃ ያድጋል፡፡ |
80 |
North Capitol Street |
እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው የጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ሰዓታት በየአውቶብሶቹ መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት ከ8.5 ወደ 10 ደቂቃ ያድጋል፡፡ |
90, 92 |
U Street – Garfield |
እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው የጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ሰዓታት በየአውቶብሶቹ መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት ከ4 ወደ 4.5 ደቂቃ የሚያድግ ሲሆን እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው የከሰዓት በኋላው ክፍለ ጊዜ በየአውቶብሶቹ መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት ደግሞ ከ5 ወደ 5.5 ደቂቃ ያድጋል፡፡ |
H2, H3, H4 |
Crosstown |
እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው የጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ሰዓታት በየአውቶብሶቹ መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት ከ5 ወደ 5.5 ደቂቃ የሚያድግ ሲሆን እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው የከሰዓት በኋላው ክፍለ ጊዜ በየአውቶብሶቹ መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት ደግሞ ከ8.5 ወደ 10 ደቂቃ ያድጋል፡፡ |
H6 |
Brookland – Fort Lincoln |
እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው ሰዓታት በየአውቶብሶቹ መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት ከ10 ወደ 14 ደቂቃ የሚያድግ ሲሆን በእኩለ ቀን ደግሞ ከ15 ወደ 20 ደቂቃ ያድጋል፡፡ |
N2, N3, N4 |
Massachusetts Avenue |
እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው የከሰዓት በኋላው ክፍለ ጊዜ በየአውቶብሶቹ መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት ከ6 ወደ 7 ደቂቃ ያድጋል፡፡ |
S2, S4 |
16th Street |
እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው ሰዓታት በየአውቶብሶቹ መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት ከ4 ወደ 4.5 ደቂቃ ያድጋል፡፡ |
V7, V9 |
Minnesota Avenue – M Street |
እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው ሰዓታት በየአውቶብሶቹ መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት ከ8 ወደ 9 ደቂቃ ያድጋል፡፡ |
X2 |
Benning Road – H Street |
እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው ሰዓታት በየአውቶብሶቹ መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት ከ6.8 ወደ 7.5 ደቂቃ ያድጋል፡፡. |
Maryland |
||
A12 |
M. L. King Jr. Highway |
እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው ሰዓታት በየአውቶብሶቹ መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት ከ20 ወደ 25 ደቂቃ ያድጋል፡፡ |
J11, J12 |
Marlboro Pike |
እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው ሰዓታት በየአውቶብሶቹ መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት ከ23 ወደ 31 ደቂቃ ያድጋል፡፡ |
Z9, Z29 |
Laurel – Burtonsville Express |
እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው የጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ሰዓታት በየአውቶብሶቹ መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት በእያንዳንዱ የጉዞ መስመር ከ20 ወደ 30 ደቂቃ ያድጋል፡፡ |
Z11, Z13 |
Greencastle – Briggs Chaney Express |
እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው ሰዓታት በZ11 አውቶብሶች መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት ከ10 ወደ 15 ደቂቃ ያድጋል፡፡ |
Virginia |
||
7A, 7E, 7F |
Lincolnia – North Fairlington |
7A,F፦ ከምሽቱ ከ8 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት በየአውቶብሶቹ መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት ከ15 ወደ 30 ደቂቃ ያድጋል፡፡ 7E፦ እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው የጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ሰዓታት በየአውቶብሶቹ መካከል ያለው የጊዜ ክፍተት ከ4 ወደ 7.5 ደቂቃ የሚያድግ ሲሆን እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው የከሰዓት በኋላው ክፍለ ጊዜ ደግሞ ከ7.5 ወደ 10 ደቂቃ ያድጋል፡፡ |
|
|
|
በRide On ፋንታ በMetrobus የሚካሄድ የሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ስምሪት (ሜትሮባስ (Metrobus) በሳምንቱ ቀናት የሚሰጠውን አገልግሎት ለመቀጠል፡፡) |
||
የጉዞ መስመር(ሮች) |
የመስመር ስም |
ቀን (ቀናት) |
L8 |
Connecticut Avenue – Maryland |
ቅዳሜና እሁድ፡፡ በRide On የሚሰጠው ዓይነት አገልግሎት፡፡ |
T2 |
River Road |
ቅዳሜና እሁድ፡፡ በRide On የሚሰጠው ዓይነት አገልግሎት፡፡ |
Z2 |
Colesville – Ashton |
ቅዳሜ፡፡ በRide On የሚሰጠው ዓይነት አገልግሎት፡፡ (እሁድ አግገልግሎት አይሰጥም፡፡) |