Genocide Watch calls on UN to initiate action against Meles

First Lady Makes it to EFFORT’s Helm

አዜብ ስብሀትን አሸነፉ

የስብሀትን ቦታ ተረክበው የኤፈርት ም/ሊቀመንበር ሆኑ
ባንድ ወቅት ህወሓትን “ከሴት ቀሚስ ነጻ ባላወጣ እኔ ስብሐት አይደለሁም” ብለዋል የተባሉት አቦይ ስብሐት ነጋ የሆነላቸው አይመስሉም። ምንክያቱም የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ቀደም ሲል አቶ ስዬ አብርሃ ኋላም አላይ አቦይ ስብሐት ነጋ ይመሩት የነበረውን የግዙፍ ድርጅት መንበረ ሥልጣን ተረክበዋል። በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ውስጥ ካሉት ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች አንዱ ተደርጎ የሚወሰደውንና ቢሊዮን ዶላሮች የሚንቀሳቀሰውን የ ኤፈርት ድርጅት ም/ሊቀመንበር ሆነው መሾማቸውን ፎርቹን ጋዜጣ በትላንትናው እትሙ ዘግቧል። በአቦይ ስብሀትና በወ/ሮ አዜብ መካከል በየጊዜው በርካታ አለመግባባቶች መኖራቸውና ግጭቶች እየተካረሩ መምጣታቸውንም ሲነገርና ሲዘገብ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን በድርጅቱ ውስጥ ከፍተኛውን ቦታ የነበራቸው አቦይ ስብሐት ነጋ ከተለያዩ ኃላፊነቶች እየተገለሉ እንደመጡ ተሰምቷል። የድርጅቱ ሊቀመንበር ተብለው በቦታው ለይስሙላ የተቀመጡት አንድ እጃቸውን በውጊያ ያጡት አቶ አባዲ ዘሙ ቀደም ሲል የእርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚ ኮሚሽን ም/ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩና ከአዲስ አበባ ተነስተው ትግራይ ተመድበው በተለያዩ ኃላፊነቶች ሲሰሩ የቆዩ ሰው ናቸው ። የሜጋ ሥራ አስኪያጅና በፓርላማው የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ መሆናቸው ይታወቃል። የኤፈርትን ሹመት አስመልክቶ ፎርቹን ያወጣውን ዘገባ እዚህ ያገኙታል

ይበልጥ የተቸገረችው ኢትዮጵያ የበለጠውን እርዳታ ታገኛለች
የአውሮፓ ህብረት ሰሞኑን በድህነት ለሚማቅቁ አገር አርሶ አደሮች መርጃ የሚሆን 314 ሚሊዮን ዩሮ ለመስጠት መወሰኑን ሲገልጽ ከዚህ ውስጥ ኢትዮጵያ ትልቁን 45.5ሚሊዮን ዩሮ እንደምታገኝ ህብረቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ከኢትዮጵያ ቀጥሎ ኮንጎ 40.6 ሚሊዮን ሲያገኙ ፍልስጥ ኤም ደግሞ 39.7ሚሊዮኢን እንደሚያገኙ ገልጿል።(EUbusiness.com)

  • በሠፈራው መርሃ ግብር – ጎንደር ትግራይ ሄዶ ቢሠፍር ምን አለበት?
  • ወይ ቤተመንግሥቱን ወይ ልመናውን ተውልን!
    ልመና በህግ እንዲከለከል በፓርላማ ተጠየቀ
  • ተከሳሹ የእነ ወ/ሮ አዜብ ጠንቋይ እያነጋገረ ነው
    የጠንቋዩ ሾፌር ጎይቶም መሀሪ ምርመራ ላይ እንዳለ ሞተ ተባለ
  • Leave a Reply

    Photo Gallery

    Designed by Nebxstudios