ተከሳሹ የእነ ወ/ሮ አዜብ ጠንቋይ እያነጋገረ ነው
የጠንቋዩ ሾፌር ጎይቶም መሀሪ ምርመራ ላይ እንዳለ ሞተ ተባለ

ሰሞኑን ታዋቂ አርቲስቶች፣ አትሌቶች፣ ሚሊየነሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ( እነ ወ/ሮ አዜብ መስፍን፣ ጄኔራል ሳሞራ የኑስና አቶ ተፈራ ዋልዋን) ጨምሮ የኢህአዴግ መከላከያ ሠራዊት አባላት እየተገኙ ያመልኩታል የተባለው ጠንቋይ በቁጥጥር ውሏል።፣ታምራት ገለታ (አባባ ተአምራት) የሚባለው ፣ በግድያና በማጭበርበር ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት መቅረቡና ጉዳዩም ብዙ ነገር መነካካቱ ቀርቶ በተቃራኒው መደፋፈኑ እየተነገረ ነው። የምስክሮችን ቃል ባጠናቀረው የክስ መዝገብ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ጨምሮ የጦሩ ኤታማዦር ሹም የሆኑትን ጄነራል ሳሞራ የኑስን አቶ ተፈራ ዋልዋና ሌሎችም የተጠቀሱ ቢሆንም በችሎቱ ስማቸው አልተደመጠም። እነሱን ብቻ ሳይሆን በርካታ ታዋቂ አርቲስቶችንና አትሌቶችን ስም ያነካካል የሚል ስጋት እንዲፈጠር የተወሰኑ የቪዲዮ ምስሎችን በማሳየት ማስፈራራት መፈጸሙ ተነግሯል። በመሆኑም ለአመል የተመረጡት አርቲስቶች ብቻ ስማቸው በዘገባዎችም ሆነ በፍ/ቤቱ ችሎት እንዲጠቀስ መደረጉ እየተነገረ ነው። ዜናው አፈትልኮ ወጥቶ ሌላ ብዙ ጣጣ ሳያመጣ ከወዲሁ እንዲገታ በዚህ ዙሪያ ተልፈስፍሶ የተጠናቀረው ዘገባ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተላለፈ ሲሆን አዲስ አበባ ውስጥም በሬዲዮና በተለያዩ ጋዜጦች ጥግ ጥጉን የሄዱ ዘገባዎች ወጥተዋል። ከጠንቋዩ ጋር ከተያዙ ሰዎች መካከል ሾፌርና የቅርብ አማካሪ ባለሟል የነበረው አቶ ጎይቶም መሀመሪ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ሞቶ መገኘቱ ተዘግቧል። የተሻለ ዘገባ ይዞ የወጣውን የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገባ እዚህጋ ያንብቡ።

Leave a Reply

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios