ኢትዮጵያ ጄነሬተር መከራየት ጀመረች-

በመላው አገሪቱ የተከሰተውን የ ኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ለመቋቋም መንግሥት በ558 ሚሊዮን ብር ኪራይ ከውጪ ያስገባቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጀኔሬተሮች ሥራ ጀመሩ፡፡
አንድ የኢትዮጵያ አሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ኃላፊ ከትናንት በስትያ ለመንግሥት የዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት በአገሪቱ የተፈጠረውን የኃይል አቅርቦት ችግር ለማቃለል በናዝሬትና ደብረዘይት ከተሞች የተተከሉ የዲዚል ጀኔሬተሮች አገልግሎት እየሰጡ ናቸው።
ጄኔሬተሮቹ 60 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላቸውና ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት አገልግሎት ለመስጠት በኪራይ መምጣታቸውም ተነግሯል።
የአገሪቱ የኃይል አቅርቦት ችግር በአጭር ጊዜ ውስጥ የማይቃለል ከሆነ፤ የጄኔሬተሮቹ የቆይታ ጊዜ ሊራዘም እንደሚችልም አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡
በናዝሬት የተተከለው ጄኔሬተር አግሪኮ ከተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ ፣በደብረዘይት ከተማ የተተከለው ደግሞ ኢነርጂስት ከተባለ የኔዘርላንድ ኩባንያ መምጣቱ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ከራሷ ተርፋ እንደኬንያና ሱዳን ለመሳሰሉ የውጭ አገራት በቅርቡ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈል ትጀምራለች ተብሎ ሲነገር መቆየቱ ይታወሳል።

Leave a Reply

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios