ህግ እና ኮሙዪኒቲያችን

በቸልተኝነት የሚደርስ የመኪና አደጋና ሕግ

ከቸልተኝነት ጋር ተያይዞ በግለሰብ ላይ የሚደርስ ጉዳት በተለያየ ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። የመጀመሪያው ጥፋቱን ያጠፋው አካል በግዴለሽነት የተነሳ ቀጥተኛ የሆነን አደጋ ሰውና ንብረት ላይ ሲያደርስ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ኃላፊነትን ካለመወጣት ጋር ተያይዞ ላይፈጠር ይችል የነበረን አደጋ ሳይከላከላል ሲቀር ነው። ከቸልተኝነት ጋር ተያይዘው ከሚጠቀሱ አደጋዎች መካከል ተንሸራቶ መውድቅ፣ የአዛውንቶች ማረፊያ ውስጥ የሚደርስ ማንናውም በደልና ቸልተኝነት የመኪና አደጋ በሐኪም ስህተት ወይም በቂ ጥንቃቄ ካለማድረግ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ሞት ወይም የአ እምሮ ጉዳትና፣ በሥራ ቦታ ላይ ከስራችን ጋር ተያይዞ የሚደርስ ጉዳት ይገኙበታል። አደጋ የደረሰበት ግለሰብ በካሉ ላይ ከደረሰበት ጉዳት በተጨማሪ፣ በ አእምሮው ላይ መቃወስ ደርሶ ህይወቱን ሊያጨልምበት ይችላል።
በግልሰብ ላይ ተመሳሳይ የሆነ ጉዳት ከሚያደርሱ ምክንያቶች መካከል በጣም የተለመደው የመኪና አደጋ ነው። በአሜሪካ ውስጥ ከ30 እስከ 33 ዓመት መካከል ለሚገኙ ወጣቶች ሞት ዋነኛ መንስ ኤ ነው። ናሽናል ሃይዌ የትራፊክ ደህንነት ቦርድ ባወጣው ሪፖርት መሰረት በ2005 ብቻ 6ሚሊዮን በላይ በሚሆኑ የመኪና አደጋዎች ምክንያት 43ሺ443 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ ሲሆን 2ሚሊዮን 699ሺ ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ማንኛውም ሰው በሌላ ግለሰብ ቸልተኝነት የተነሳ በተፈጠረ የመኪና አደጋ ጉዳት ቢደርስበት የገንዘብም ሆነ የሞራል ካሳ የመጠየቅ ሙሉ መብት አለው። ሕጉ ጥፋተኛ ወገንን ለማንኛውም ከህክምና ጋር ተያይዞ ለወጣ ወጪና እንዲሁም ወደፊት ሊወጣ ለሚችል ወጪ ተጠያቂ ከማድረጉም በተጨማሪ የተጎዳው ወገን ለደረሰበት ማንኛውም ጉዳት ካሳ እንዲጠይቅ ይፈቅዳል። ለምሳሌ የንብረት መጥፋት፣ ማንኛውም በኑሮ ላይ የፈጠረው ጫና፣ እንዲሁም የገቢ መቋረጥ ወይም መቀነስ ተለክቶ የተመጣጠነ ካሳ እንዲከፍል ያዛል።

የመኪና አደጋ ሲደርስ መወሰድ የሚገባቸው እርምጃዎች

1. አደጋ ከተፈጠረ በኋላ መኪናውን ማቆም አስፈላጊ ነው። ምንም እንኳ ሙሉ ጥፋተኛ ሌላውን ወገን ቢሆንም አደጋ ካደረሰ በኋላ ጥሎ መሄድ ወንጀል ነው።
2. ምንም እንኳ አስደንጋጭ ሁኔታ ቢሆንም ለመረጋጋት መሞከር ከአደጋ ነጻ መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ ከመኪና መውረድ።
3. ማንኛውም ሰው ከተጎዳ 911 ደውሎ በ ት እግስት ፖሊሲ እስኪመጣ መጠባበቅ አደጋው እንዴት እንደደረሰ እና የደረሰውን ጉዳት ለመረዳት መሞከር።
4. የሌላኛው መኪና ሹፌር ስምና አድራሻ፣ የመድህን ድርጅቱን ስምና መረጃ፣ የመንጃ ፈቃድ ቁጥር፣ እና የመሳሰሉትን መረጃዎችን መቀበል ተመሳሳይ የሆነን የራስ መረጃ መስጠት። እንዲሁም የሌሎች ተሳፋሪዎችንና ምስክሮችን ስምና አድራሻ መቀበል።
5. በዚያን ጊዜ ምንም ዓይነት አስተያየት ከመስጠት መቆጠብ ያስፈልጋል። ፖሊሲ ከመጣ በኋላ ራስን ተጠያቂ ሳያደርጉ የተፈጠረውን ለፖሊሱ ማስረዳት። በዚያን ጊዜ ለአደጋው ኃላፊነትን መውሰድ በህግ የራሱ የሆነ የተወሳሰበ ችግር ስላለው ራስን ተጠያቂ ከማድረግ መቆጠብ ያስፈልጋል።
6. ለፖሊስ አስፈላጊውን ትብብር ማድረግና እስከተፈለገው ጊዜ ድረስ በአካባቢው መቆየት። አደጋው እንዴት እንደተፈጠረ፣ የነበረውን የትራፊክ እንቅስቃሴ እና የመንገዱን ሁኔታ የመኪናውን ፍጥነትና የነበረውን የአየር ሁኔታ በሃስብ መቅረጽ ወይም በጽሁፍ ማስፈር ጥሩ ሀሳብ ነው።
አደጋ የደረሰበት ሰው ህመም እንደተሰማው ወደ ሀኪም ቤት መሄድ አለበት። የህመም ስሜት እስከተሰማዎት ወይም አደጋው ከፍተኛ ከሆነ፣ አደጋው እንደተፈጠረ ወዲያውኑ አለማወላወል ወደ ሐኪም ቤት ድንገተኛ ክፍል ውሰዱኝ ብለው ይጠይቁ። አደጋው ከደረሰ በኋላ ከሆነ ደግሞ ሕመም የተሰማዎት “ Claim # “ እንኳ ባይኖርዎ የራስዎን ሐኪም ጋር ወይም ሆስፒታል ወይም ማንኛውም የጤና አገልግሎት መስጫ ቦታ ሄደው ይታከሙ። ይህ ለራስዎ የ አእምሮ እረፍትም ሆነ ከዚያ በኋላ ጉዳዩ ሲታይ ለደረሰብዎ ጉዳት ክብደት ይሰጠዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ሊታሰብ የሚገባው ጉዳይ ቢኖር ለወጣው የህክምና ወጪን የጉዳት ካሳ ሌላኛው ወገን ተጠያቂ የሚሆነው ሙሉ ለሙሉ ጥፋተኛ ከሆነ ብቻ ነው። ለአደጋው መከሰት ምክንያት የእርሶ ጥፋት ከሆነ ወይም አደጋው እንዲፈጠር ሚና ከተጫወቱ የሌላኛው ወገን ኢንሹራንስ ወጪዎን አይሸፍንም ምንም ካሳ አያገኙም።
አደጋ ካጋጠመ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የመድህን ድርጅት ወኪሎች አደጋ የደረሰበትን ወገን ጋር በስልክ በመደወል ጉዳዩን በአጭሩና በቀላሉ ለመደምደም ጥረት የማድረጋቸው ሁኔታ የተለመደ ነው። ይህን የሚያደርጉበት ምክንያት ገና የተጎዳው ሰው ጠበቃ ሳይዝ በአናሳ ገንዘብ ጉዳዩን ለመጨርስ ነው። ስለዚህም የራስ ጠበቃ ሳይዙ ከመድህን ድርጅት ወኪሎች ጋር መደራደር የኢንሹራንስ ድርጅት ወጥመድ ውስጥ መውደቅ ነው። ምንም ያህል መልካም መስለው ቢቀርቡም የኢንሹራንስ ድርጅቶች ዓላማ ከእርስዎ ዓላማ ጋር ፈጽሞ ተጻጻሪ ነው። የኢንሹራንስ ድርጅት ወኪሎች ሥራቸው ለሚሠሩበት ድርጅት ወጪ መቀነስ ሰለሆነ እርስዎ የሚገባዎትን ካሳ አለመክፈል ትርፋማነታቸውን ይጨምረዋል ማለት ነው።

Leave a Reply

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios