የሳምንቱ ጥያቄ

ምርጫው ምርጫ ይጠይቃል?
በመጪው 2002 የሚካሄደው ምርጫ በተመለከተ “መንግሥት ሂደቱ ሰላማዊ ግልጽ ፣ ነጻና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲካሄድ አስፈላጊውን ጥረት እንደሚያደርግ” ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ወጣቶች ጋር ባደረጉት ውይይት መናገራቸው ተዘግቧል።ፓርቲያቸው በዚያ ምርጫ ብቻውን መወዳደሩም ሆነ አሸነፍኩ ማለቱ የሚጠበቅ ነው። ዐመል ሆኖበት ኢህአዴግ ከራሱ ጋር የሚያደርገውን የምርጫ ውድድር ሳይቀር ካላጭበረበር በስተቀር አሸናፊነቱ እንደተገመተ ነው። ለምርጫ ሊቀርቡ ይችላሉ የሚላቸውን ተፎካካሪ ድርጅቶችና መሪዎቻቸውን የማሰርና የማስፈራራት ድርጅቶቻቸንውም የማዳካም ሥራም እየሠራ መሆኑ ይታያል። የዚያኑ ያህልም ራሱን የማጠናከር ሥራ እየሠራ ሲሆን ከተለያዩ የህብረተረሰብ ክፍሎች ጋር እየተገናኘ ደጋፊዎችን ለማብዛት እየሠራ መሆኑ ይታያል።በተቃዋሚ ድርጅቶች በኩልስ ምን አለ? ይህ የሳምንቱ ጥያቄ ይመስላል።

ተወደደም ተጣላም በኢትዮጵያ ቀጣዩ ብሄራዊ ምርጫ መደረጉ አይቀርም። የሚቀጥለው ምርጫ ምን ይሆናል? ወይስ ሲደርስ ይታሰብበታል? ምርጫውን መሳተፍ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም? ያስፈልጋል ከተባለ ለምን? አያስፈልግምም ከተባለ ለምን? መሳተፍ አለመሳተፍን ከወዲሁ መወሰን ይጠቅማል አይጠቅምም? ለመሆኑ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችሉ አስፈላጊ ምቹ ሁኔታዎች አሉ? ምርጫውስ የማይደረግ ከሆነ ሌላው አማራጭ ምን ይሆናል? በምርጫው ለመሳተፍ ብቻ ሳይሆን ላለመሳተፍም ዝግጅት ያስፈልጋል አያስፈልግም? ምርጫውን በተሳትፎአቸው ለማጀብ የሚቋቋሙ ወይም እንዲሳተፉ የሚገደዱ ተቃዋሚም ሆኑ መንግሥት አደር ተቃዋሚዎች ብቅ ብለው “መጠነኛ” ቅሬታ የሚቀርብበትን ምርጫን ቢያደርጉ መፍትሄው ምን ይሆናል? የውጭ ዲፕሎማትና ታዛቢዎችም እንደተለመደው “ምርጫው በ እርግጥ አንዳንድ ችግሮች አሉበት ግን አጠቃላዩ ሁኔታ ሲታይ አበረታችና ተስፋ ሰጪ ነው ” የሚል ምስክርነት ቢሰጡ ምን ይደረጋል?

Leave a Reply

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios