ኢህአዴግ ሊቀመንበርና ምክትሉን ነገና ከነገ ወዲያ ይመርጣል

ኢህአዴግ የግንባሩን ሊቀመንበር ነገና ከነገ ወዲያ በሚያካሂደው ስብሰባ ይሰይማል። ጽህፈቱ ቤቱ እንዳስታወቀው የምክር ቤቱ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መስከረም 4 እና 5 ቀን 2005 ዓ.ም ስብሰባውን በማድረግ ፥ አቶ መለስን የሚተካ የግንባሩን ሊቀመንበር እንዲሁም ምክትል ሊቀመንበር የሚሰይም ሲሆን ፥ ሌሎች ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችንም ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
የኢሕአዴግ ምክር ቤት ከአራቱ አባል ድርጅቶች  የተሰየሙ 180 አባላት ያሉት ሲሆን በሁለቱ ጉባዔዎች መካከል የግንባሩ ከፍተኛ የሥልጣን አካል ሆኖ እንደሚያገለግልም አመልክቷል፡፡

Leave a Reply

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios