በኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሰኔ 2001 ዓ.ም ለነዳጅ ምርቶች አዲስ የችርቻሮ ዋጋ ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡ሚኒስቴሩ ዛሬ እንዳስታወቀው የዋጋ ጭማሪው ከነገ ሰኞ ሜይ 8/2009 ጀምሮ በነዳጅ ማደያዎች ተግባራዊ ይሆናል ።
የዋጋ ክለሳው በነጭ ናፍታ፣ በኢታኖል- በቤንዚን ድብልቅ፣ በኬሮሲን፣ በቀላል ጥቁር ናፍጣ ፣ በከባድ ጥቁር ናፍጣ ፣ በአውሮፕላን ነዳጅ ላይ ነው፡፡
በመሆኑም ነጭ ናፍታ 7ብር ከ49 ፣ ኢታኖል ቤንዚን ድብልቅ 8 ብር ከ96 ሳንቲም፣ ኬሮሲን 6ብር ከ07 ሳንቲም፣ በሊትር እንዲሸጥ ተወስኗል ።
እንዲሁም ቀላል ጥቁር ናፍታ 6ብር ከ69ሳንቲም ፣ ከባድ ጥቁር ናፍታ 6ብር ከ15 ሳንቲም እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ 8ብር ከ04 በሊትር እንዲሸጡ መወሰኑን አስታውቋል።

Leave a Reply

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios