የተፈቱት ሰዎች እዚያው እሰርቤት በር ላይ ተመልሰው ታሰሩ
በቅርቡ ታስረው የነበሩት የስታር ቢዝነስ ግሩፕ ሰዎች ዛሬ ማለዳውን እንዲፈቱ ከተወሰነ በኋላ ከእስር ቤት እንደወጡ እዚያው በሩ ላይ ይጠበቋቸው በነበሩ የማእከላዊ ወንጀል ምርመራ ፖሊስ አባላት ተወስደው መታሰራቸው ተነገረ። ፍርድ ቤት እስረኞቹ እንዲፈቱ የወሰነው ትላንት ሲሆን ወዲያውኑ መለቀቅ ሲገባቸው ሰው የለም በሚል እዚያው እስር ቤት እንዲያድሩ ተደርገዋል። አብረዋቸው ከተፈቱ ሰዎች ውስጥ እነ አቶ ተመስገን መሀሪ ግን ተመልሰው አልታሰሩም። እነሱን የጫነችው መኪና ለጊዜው በሰላም አልፋ የሄደች መሆኑን የዘኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል።

Leave a Reply

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios