Interview: Berhanu Nega, Ginbot 7

ጥላሁንን የዘከረ ዝግጅት በዋሽግንተን ዲሲ ተደረገ
የአርቲስት ዶክተር ጥላሁን ገሠሠን ህይወትና ሥራዎች የሚዘክር ዝግጅት ትናንት እሁድ በዋሽንግተን ዲሲ ዋርድማን ሜሪዬት ሆቴል ተከናውኗል። በዝግጅቱ ላይ ድንገት ከኢትዮጵያ መጥቶ የተገኘው አርቲስት መሀሙድ አህመድን ጨምሮ ታሞራት ሞላና ሌሎች በርካታ ድምጻዊውያንና ሙዚቀኞች ተገኝተዋል። የመታሰቢያ ፀሎትና የጉዞ ፍትሐቱ አርቲስት ጥላሁና አባል በሆነበት የደብረ ገነት መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን ካህናት የተፈጸመለት ሲሆን የተለያዩ ተናጋሪዎች በጥላሁን ዙሪያ ንግግርና ግጥሞችን አሰምተዋል።አርቲስት ዓለም ፀሐይ ወዳጆም ለጥላህን ክብር በኢትዮጵያ የተከናወነውን ዝግጅት በፊልም ከማቅረብ ጋር የጥላሁንን የህይወት ታሪክ አሰምታለች። እንደወትሮው ሁሉ የሚጠበቀውና ዝግጅቱን በዋነኝነት ያደመወቀውና ብዙዎችን ያስለቀሰውን ሥራ ይዞ የቀረበው ታማኝ በየነ ነበር።ታማኝ ባቀረበው የፊልም ዝግጅት በኢትዮጵያ የሙዚቃን ታሪክ አጀማመር አንስቶ የጥላሁን ገሠሠን ወደሙዚቃ ዓለም መግባት በማውሳት በህይወት ዘመኑና በመድረክ ዓለሙ ያሳላፋቸውን ጉዞዎች የሚያሳይ የፊልም ዝግጅት አቅርቧል።ከጥላሁን ገሠሠ ቤተሰቦችም የጥላሁን ባለቤት የወ/ሮ ሮማን እህት ባለቤት የሆኑት አቶ ጌዲዮን ቤተሰቡን በመወከል አዘጋጅተው የመጡትን ንግግር አሰምተዋል።ዝርዝሩን በሚቀጥለው የዘኢትዮጵያ ጋዜጣ እትም ይዘን እንቀርባለን።

Leave a Reply

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios