BREAKING NEWS -Tilahun Gesesse passes away

(Photo Mekonen Ayale, 2006 Zethiopia)

The renowned and veteran Ethiopian vocalist, Tilahun Gessesse, passed away late on Sunday. Tilahun, before he came back home few days ago for Easter holiday, was receiving medical treatment abroad. Tilahun, 68, passed away when he was being taken to hospital after he felt sick on Sunday April 19, 2009.

Tilahun passed away when he was being taken to hospital after he felt sick yesterday night. The legendary Ethiopian great received an Honorary Doctorate Degree from Addis Ababa University, in appreciation of his contribution to Ethiopian music.

He has also received an award for his lifetime achievements from the Ethiopian Fine Art and Mass Media Prize Trust.(walta)

ጥላሁን ገሠሠ አረፈ

ላለፉት 50 ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ ሙዚቃ መድረክ ነግሦ የቆየው ጥላሁን ገሠሠ እሁድ ሌሊት ለሰኞ አጥቢያ ከዚህ ዓለም መለየቱን ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ጥላሁን በ68 ዓመቱ ንጋት ላይ ከዚህ ዓለም በድንገት በሞት የተለየው ሌሊቱን ከአሜሪካ ከገባ በኋላ መሆኑን ቤተሰቦቹ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ በቁጥር አንድ ደረጃ የሚቀመጠው ታዋቂ አርቲስት ከወይዘሮ ጌጤ ጉርሙና ከአቶ ገሠሠ ገብረ ኪዳን በ1933 በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ልዩ ስሙ ፊት በር በተባለው ሰፈር ተወለደ።

ዕድሜው 14 ዓመት ሲሞላ ትምህርቱን በወሊሶ ከተማ ለመከታተል ሄደ።ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ከዚያ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ የሙዚቃ ሥራውን መጀመሩን የሕይወት ታሪኩ ያመለክታል።

ጥላሁን በሕይወት ዘመኑ በሙዚቃው ዓለም ባበረከተው አስተዋጽኦ በርካታ ሽልማቶች ያገኘ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ማግኘቱንም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

Leave a Reply

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios