Supporters mourn PM’s death

የአቶ መለስ ደጋፊዎች ሐዘናቸውን እየገለጹ ነው
 watch Live

መከላከያ ለመንግሥቱና ህግመንግሥቱ መቆሙን ገለጸ
(ዘኢትዮጵያ) የመከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ በጠቅላይሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን በመግለጽ ሠራዊቱ ለህግመንግሥቱና ለመንግሥቱ በጽናት እንደሚቆም አስታውቋል።
መከላከያ ባወጣው መግለጫ ሠራዊቱ እንደ ከዚሁ ቀደሙ ሁሉ አሁንም አገሪቱ ለምትመራበት ሕገ መንግስትና ሕገ መንግስታዊ ስርዓት ያለንን የማያወላዳ ታማኝነት እየገለጸን ሕገ መንግስታዊና ወቅታዊ ተልዕኮቸውን ከምንጊዜውም በላይ በላቀ ደረጃ ለመፈጸም ዝግጅነታችንን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝቦችና ለመንግስታችን እናረጋግጣለን ብሏል፡፡
ታላቁ መሪያችንመላው ሕዝባችን የአገራችን ወዳጆች በነበራቸው የአመራር ብቃት የተመሰከረላቸው ታላቅ መሪ ነበሩ” በማለትም ለአቶ መለስ ዜናዊ የነበረውን አክብሮትና ፍቅር ገልጿል።  
የሚኒስትሮች ም/ቤት ባወጣው መግለጫ “በአገሪቱ  ህገ መንግስት መሰረት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ  የሚኒስትሮች ምክር ቤትን እየመሩ  ይቀጥላሉ ብሏል ።”
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት፣ ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦን በሒልተን ሆቴል ዛሬ ማለዳ በሰጡት መግለጫ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን “በሙሉ ሥልጣን” አገሪቱን እንደሚመሩ አስታውቋል፡፡
በሚቀጥለው መስከረም መጨረሻ የሚሰበሰበው (አንዳንዶች ከዚያ በፊትም በአስቸኳይ ይሰበባሰባል እያሉ ቢሆንም) ፓርላማው የሚቀጥለውን ጠቅላይ ሚኒስትር (“አቶ ኃማርያም ላይሆኑም ይችላሉ ) ሊመርጥ እንደሚችል ተነግሯል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን የቀብር ሥነ ሥርዓት የሚያስፈጽም ሰባት አባላት ያሉት ብሔራዊ ምክር ቤት መቋቋሙንም አቶ በረከት አስረድተዋል፡፡
መንግሥት በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ትናንት ከምሽቱ 5፡40 ላይ ማረፋቸውን የገለጸ ሲሆን፣ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ስለ ሕመማቸውና አማሟታቸው ዝርዝር መግለጫ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡
የቀብር ሥነ ሥርዓቱ እስኪፈጸም ድረስ ከዛሬ ጀምሮ  ብሔራዊ የሐዘን ቀን ሲታወጅ የአገሪቱ ሰንደቅ ዓላማም ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብ አቶ በረከት አስታውቀዋል፡፡ (ዘኢትዮጵያ)
አቶ ኒቆዲሞስ ቤት እየተለቀሰ ነው
አቶ መለስን ብሔራዊ የሐዘን ሥነ ሥር ዓት እስኪደርስ ወይንም ቤተመንግስት ለመግባት እድሉ የሌላቸው ሰዎች ቦሌ መንገድ በሚገኘው የአቶ ኒቆዲስ ዜናዊ ቤት እየደረሱ መሆናቸው ተነግሯል። ቦሌ መንገድ ከቦሌ ማተሚያ ቤት ጀርባ በሚገኘው የአቶ ኒቆዲሞስ ዜናዊ ቤት በረጅም መንገድ ላይ የተዘረጋው ትልቅ ድንኳን ተተክሎ ደራሽና ለቀስተኞችን እያስተናገዱ መሆኑ ተሰምቷል። ከደቂቃዎች በኋላ ኢትዮጵያ ይገባል የተባለውን የጠቅላይ ምኒስትሩን አስክሬን ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለመቀበል የሚጠባበቁ ሰዎች በቦታው  መገኘታቸውም ተገልጿል። ለከፍተኛ ባለሥልጣናትና ልዩ እንግዶች ብቻ በሚፈቀደው የቪ አይፒ ላውንጅ ብቻ ከ500 በላይ የሚደርሱ ሰዎች መታየታቸውን ምንጮች ገልጸዋል። በብዙ ሺዎች ደግሞ የሚቆጠሩት ከውጭ እየተጠባበቁ ነው።

Leave a Reply

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios