ደግሞ እንደገና ተለወጠ! በረከት ስም ቢቀይሩ ያው በረከት ናቸው
የኢት. ሬድዮና ቴሊቪዥን ስም መዋቅርና ቦታ እየለወጡ ነው። የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን አንዴ ድርጅት አንዴ ኢንተርፕራይዝ አንዴ መምሪያ እየተባሉ ሲጠሩ ቆይተው አሁን ደግሞ ኮርፖሬሽን ሊባሉ መሆኑ ተነግሯል። አንዴ አቡነ ጴጥሮስ፣ አንዴ ማዘጋጃ ቤት፣ አንዴ ጅማ መንገድ ብስራተ ወንጌል፣ አንዴ ብሔራዊ ቴአትር አካባቢ ሲዘዋወሩ ቆይተዋል። አሁን ደግሞ አንድ ላይ ሆነው መከላከያ ሚኒስትር ፊት ለፊት በሚገኘውና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ህንጻ ላይ አንድ ላይ እንዲጠቃለሉ እየተወሰነ ነው። ስማቸውም የኢትዮጵያ ቴሌቪዝንና ሬዲዮ መሆኑ ቀርቶ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሊባል ነው።እነዚህ ሁለት የሬዲዮና የቴሌቪዥን ተቋማት አቶ በረከትን እየተከተሉ ነው።አቶ በረከት መጀመሪያ የማስታወቂያ ሚኒስትር ሲባሉ የሚኒስቴር መምሪያ ተባሉ። አቶ በረከት የማስታወቂያ ሚንስቴር ቦርድ ሊቀመንበር ሲሆኑ ድርጅት ሆኑ። አቶ በረከት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ ሲሆኑ ኢንተርፕርያዝ ምንትስ ተባሉ። አሁን ደግሞ በቅርቡ የcommunication affairs office ሚኒስትር ሆነው ሲሾሙ አቶ በረከት ሬዲዮና ቴለቪዥናቸውን ኮርፖሬሽን እያሉት ነው። ለዚህ አዲሱ አደረጃጀታቸውም 200 የሚሆኑ ካድሬዎችንና ሠራተኞችን ደብረዘይት ማኔጅመንት ኢንስቲቲዩት ልከው ማሰለጠናቸውም ተነግሯል። ነገሩ እንደ ቢቢሲ መሆኑ ነው። ሰሚና ተሰሚነት ያጣው የኢትዮጵያ ቴሌቪዝንና ሬዲዮ ችግሩ የመዋቅር ወይም የስያሜ ሳይሆን ኢህአዴግ አዲስ አበባ ሲገባ ጀምሮ የዚህ ቁንጮ የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ጭምር ናቸው። ዛሬም ድረስ እንደግል ንብረታቸውና የማይለወጥ ርስት አድርገው የያዙትን ቤት መለወጥ አለመቻላቸው እየታየ ነው። በረከት ስም ቢቀይሩ ያው በረከት መሆናቸው አይቀርም።

የአንድነት አመራር አባላት ሰልፉ ሊወጡ ነው
የድርጅታቸው ሊቀመንበርና የአምባገነኑ ሥርዓት እስረኛ የሆኑት፣ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እንዲፈቱ ለመጠየቅ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አባላት ሰልፍ ለመውጣት ፈቃድ መጠየቃቸውን አዲስ አድማስ ዘግቧል። በየደረጃው ያሉ የፓርቲው አመራር አባላት ተቃውሟቸውን ለፕሬዚዳንቱና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚያቀርቡ በመግለጽ መግለጫ ያወጡ ሲሆን ሰልፉን ለማድረግ ያሰቡት ሐሙስ ሚያዝያ 1/2001 እንደሆነም አስታውቀዋል። በሰልፉ ለመሳተፍ የጠየቁት 250 የድርጅቱ የአመራር አባላት ወይዘሪት ብርቱካን ላይ የተወሰደው እርምጃ ያላግባብ መሆኑንና ይቅርታው ሊነሳ እንደማይገባ መግለጻቸው ታውቋል።

Leave a Reply

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios