“ጠ/ሚ መለስ በቤተመንግሥት እያገገሙ ነው ተባለ” አዲስ አድማስ
ሳምንታዊው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ “ከመኖሪያ ቤታቸው ሥራ ጀምረዋል” መባሉን ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሊሰጡት ታቅዶ የነበረ መግለጫ ተሰርዟል” በማለት የጻፈው ጋዜጣ “አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ከመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከአራት ባለስልጣናት ጋር ብቻ በመነጋገር እየሰሩ ናቸው ሲሉ ጠቆሙ” ብሏል።

“እኚሁ ከፍተኛ ባለስልጣን፤ ጠ/ሚ መለስ በውጭ ሀገር ሕክምናቸውን ተከታትለው ከሳምንት በፊት አዲስ አበባ እንደገቡ ጠቅሰው፤ በሁለት ኢትዮጵያዊያን ዶክተሮች ክትትል እየተደረገላቸው ነው ብለዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ከሕመማቸው በማገገም ላይ እንደሆኑና ቤተመንግስት በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ከአራት ባለሥልጣናት ጋር ብቻ በመነጋገር፣ የሚቀርብላቸውን ሪፖርት እያዳመጡ ትዕዛዝ በመስጠት ላይ ናቸው ብለው እኚሁ ከፍተኛ ባለስልጣን፡፡

አቶ መለስ ፊት ለፊት በሚታየው የአካላቸው ክፍል ላይ ምንም ዓይነት የቀዶ ሕክምና ምልክት እንደሌለ የተናገሩት እኚሁ ከፍተኛ ባለስልጣን፣ ህክምናውን ያደረጉላቸው ሐኪሞች ብዙ ከመነጋገር እና ከመሥራት እንዲቆጠቡ እንዲሁም በቂ እረፍት እንዲያደርጉ ጥብቅ ማሳሰቢያ እንደሰጧቸው አረጋግጠዋል።” ሲል ጽፏል።

“ጠ/ሚኒስትሩ ባለፈው ሣምንት በጽ/ቤታቸው አጠር ያለ መግለጫ እንዲሰጡ ታቅዶ እንደነበር እኚሁ ባለስልጣን የተናገሩ” መሆኑን ገልጾ “ከጤናቸው ጋር በተያያዘ መግለጫው ሊሰረዝ እንደቻለ ምንጮች መገመታቸውን አዲስ አድማስ ጽፏል። የአዲስ አድማስን ዘገባ ከእርግጠና ምንጮች ማረጋገጥ አልተቻለም።

Ethiopia’s Gelana wins marathon gold 

Ethiopia’s Tiki Gelana held off the Kenyan Priscah Jeptoo to win gold in a soggy Olympic women’s marathon on Sunday.

Gelana clocked 2hr 23min 7sec, an Olympic record time, finishing five seconds ahead of Jeptoo. The Russian Tatyana Petrova Arkhipova won bronze with the pre-race favourite Mary Keitany having to settle for fourth. It was Gelana’s major championship.

Leave a Reply

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios