ቴዲ አፍሮ እንደገና ይግባኝ ቀረበበት

የቴዲ አፍሮ የቅጣት ማቅለያ እንዲሻር ዐቃቤ ህግ ማመልከቱ ተዘገበ። በቴዲ አፍሮ ላይ የተወሰነው የቅጣት ማቅለያ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበትና ቀደም ሲል በከፍተኛ ፍ/ቤቱ የተሰጠውን የቅጣት ማቅለያ እንደገና በመድገም የተወሰነ ውሳኔ በመሆኑ ቅጣቱ ሊቀልለት አይገባም ሲል ዐቃቤ ህጉ ይግባኝ መጠየቁ ተነግሯል። የመንግሥት ጠበቃው ባለፈው ረቡዕ ለሰበር ችሎቱ ባስገባው ማመልከቻ መሰረት ቴዲ አፍሮ የተከራከረው ወይም ይግባኝ የጠቀየው ጥፋተኛ አይደለሁም በሚል እንጂ ቅጣቱ በዝቶብኛልና ይቀነስልኝ በሚል አይደለም። ስለዚህ ውሳኔ ባልተጠየቀበት አቤቱታ ላይ የተሰጠ ፍርድ ነው በማለት ቀደም ሲል የተፈረደው የ6 ዓመት ፍርድ ወደ ሁለት ዓመት ተቀነሶ መወሰኑ አግባብ አለመሆኑ ገልጿል።በመሆኑም ቀደም ሲል የተወሰነበት የ6 ዓመት ፍርድ የተሰጠው የድርጊቱን አፈጻጸም ግምት ውስጥ በማስገባት ስለሆነ ሌላ ተጨማሪ የቅጣት ማቅለያ ሳያስፈልገው ውሳኔው እንዲጸናበት አመልክቷል። ይግባኝ ሰሚው ችሎት ጉዳዩ ይግባኝ ያስቀርባል ወይስ አያስቀርብም የሚለውን ለማየት ለግንቦት 19/2001 ቀጠሮ መስጠቱ ተዘግቧል

Leave a Reply

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios