ኢህአዴግ ራሱን አደነቀ- ግምገማ ተቀምጧል


የኢህአዴግ ም/ቤት ስምንተኛ ድርጅታዊ ስበሰባውን ከትናንት ጀምሮ እያካሄደ ሲሆን የድርጅቱን እቅንስቃሴና አቅጣጫ እየገመገመ መሆኑ ታውቋል። በወያኔ ሓርነት ትግራይ ሊቀመንበር በአቶ መለስ ዜናዊ ሊቀመንበርነት የሚመራው የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ሪፖርት ማቅረቡም ተነግሯል። በሪፖርቱም መሠረት ነገሮች ሁሉ በተቀመጠላቸው አቅጣጫ እየተጓዙ መሆናቸው ተገልጿል። ለወደፊቱም በየደረጃው የሚገኙ መንግሥታዊና ድርጅታዊ አስፈጻሚ አካላት ትኩረት ሰጥተው እንዲቀሳቀሱባቸው የሚያስፈልጉ አቅጣጫዎች እየተነደፉ መሆኑም ተነግሯል። ባለፈው የድርጅቱ ሰባተኛ ስበሰባ ላይ የተላለፉ ውሳኔዎች ተግባራዊ በመሆናቸው ድርጅቱ ለሚቀጥለው ምርጫ ሙሉ ዝግጅት ማድረጉን፣ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶችን አከርካሪ በመሰበር አስጊ ሊሆኑ ወደማይችሉበት ደረጃ ማውረዱን፣ በነጻው ፕሬስ ስም መንግስታዊ ባልሆኑ የበጎ አድራጎት ድርጅት ስም የሚንቀሳቀሱትን የተቃዋሚ ኃይላት የሚቆጣጠርበት መፍትሔ ማበጀቱን፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ጋር መቀራረብ መፍጠሩን በማውሳት ድርጅቱ የተከተላተቻውን አቅጣጫዎች አወድሷል።

Leave a Reply

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios