ኧረ ስለ እግዜአብሄር!

ማሽላን ከወፍ እንዲጠብቅ የተቀጠረ እረኛ ወፍ ማባረሪያ ጠጠር የሚያቀብለው ሌላ እረኛ ቀጠረ ይባላል። ራስን አጓጉል ከፍ ከፍ የማድረግና ያልተገባ ሥልጣንን የመፈለግ አባዜ ከጥንት ከጧቱ የነበረ መሆኑን የሚያመላክቱ እንዲህ ዓይነት አባባሎችን አባቶች አቆይተውልናል። እንግዲህ እረኛም ምክትል እረኛ ከቀጠረ እረኝነቱን በአንድ የሥልጣን ደረጃ ከፍ የማድረግ አሳብ አለው ማለት ነው። ምክትሉ እረኛም፣ የእረኛም ምክትል አለው- ብሎ ሲያስብ፣ አንድ […]

በሚሊኒየሙ ለፍቅር እንበድ!

2000 ዓመተ ምህረት ሊሆን ነው። ሚሊኒየም መባሉ 19 መቶውን ሸኝተን 2000ውን ልንቀበል በመቃረባችን ነው። የምንቀበለው አዲስ ዓመት አይደለም። አዲስ ምእተ (መቶ) አመት ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ይህን የሽግግር ጊዜ በህይወት ያለው ሁሉ እኩል ይቀበለዋል። አገር ቤት ያለው፣ ስደት ያለው፣ ቤተመንግሥት ያለው፣ እስር ቤት ያለው፣ ዲታውም ቺስታውም ሁሉም እኩል ይቀበለዋል። ሁሉም በያለበት ሆኖ ይሸጋገረዋል። ልዩነቱን ልዩ ብሎ […]

ህዝቡም አሜን ማለት አለበት!

እውርን ምን ይቫላል? ቢሉት “ማየት” አለ ይባላል። ማየት ነው። መስማትም ይቻላል። በተለይ “አለበት” የሚል ቃል አለ። ህዝቡ አንድ መሆን “አለበት”፣ ተቃዋሚው ጠንካራ መሆን “አለበት”። ሚዲያው ነጻና ገለልተኛ መሆን “አለበት”። መንግሥትም እንዲህ ማድረግ “አለበት።” አለበት አለበት አለበት…ነው። “አለብኝ” ማለት አያስፈልግም። ብዙ ሰው ፖለቲካ ሰለማይወድ ወይም የራሱን መስዋእትነት ከፍሎ ስለጨረሰ ቀጭን መመሪያ ማስተላለፍ ይችላል። እኔ ሳልሆን ህዝቡ […]

ያን ያህል እንኳ አልሞትንም!

አንድ ምሽት ላይ ሚስት ተደብድቦና ተፈነካክቶ የመጣ ባሏን ቁስል ትጠራርጋለች። አፍንጫው፣ ከንፈሮቹ፣ ጉንጮቹ… ቆስለዋል። ወጣ ስትል ደግሞ አይኑ አጠገብ ከቅንድቡ ሥርም ቆስሏል። በዚህ ጊዜ ደንገጥ ብላ “ውይ አንተየዋ አይንህን አጥፍተውት ነበር እግዜር ለትንሽ ነው ያወጣህ” ትለዋለች። ተደብድቦ ሚስቱ ፊት የመጣው ባል በስጨት ይልና “ዝምበይ! ምን ትላለች ይቺ… ዐይኔን እስኪያጠፉት ድረስ ሞቼያለሁ እንዴ!…” አላት ይባላል። አንዳንዴ […]

ሰላም ወዳድ ረሀብተኞች!

ከረሀቡ ይልቅ ስለረሀቡ የሚወራው ሰልችቶናል – ምክንያቱም በዓይናችን ሙሉ ማንንም ቀና ብለን እንዳያይ ያደርገናል። ለአንዳንዶቻችን የረሀብ ጉዳቱ እሱ ብቻ ነው። ምክንያቱም እኛንም ከተራቡት ይደምረናል። እውነት ለመናገር አንዳንዴ እግዜር ይቅር ይበለን እንጂ የፈለገው ህዝብ እዚያ ፍግም ብሎ ወሬው እፍንፍን ተደርጎ ቢቀር የምንመኝ አንጠፋም። ሸሽተነውና አምልጠነው የመጣነው ህዝብ ጠግበን የምናድርበት አገር ድረስ ተከትሎ መጥቶ ለምን ይረብሸናል? እኛንም […]

የትንሽ ሰው አጀንዳ ትንሽ ነው

ከህግ እስካልተጣላ ድረስ፣ ማንም ያሻውን ሊል፣ የሚችልበት አግባብ ይኖረዋል። ይህ ብዙዎች የሞቱለት አገራችንም የምምትጓጓለት መብት ነው። በዚህ መደራደር አይቻልም። መደራደር የሚቻለው በምርጫችን ነው። ሰው መናገር የሚችለውን አድማጭም መስማት የሚፈልገውን ይመርጣል። ችግር የሚመጣው ተናጋሪም መናገር የማይችለውን የቀባጠረ፣ አድማጭም መስማት የማይፈልገውን ለመስማት “የተገደደ” እንደሆነ ነው። ማንም ሳያስገድደው የሚያሳምመውን ሁሉ እያሳደደ የሚሰማ ካለ ግን ጉዳዩ የህግ ሳይሆን የህክምና […]

ምን አለበት ብሎ ነገር!

ለአዲስ ዓመት አዲስ አበባ የተገኙና ዘመኑ ደስ ያላቸው ሁሉ አዲሱን ዓመት በቴሌቪዥን በተላለፈ የሸራተኑ ርችትና የምሽት ፈንጠዚያ ተቀብለዋል። ለራሳቸው ወይም ለህዝቡ እንኳን አደረሳችሁ ለመንግሥት ደግሞ “እንኳን አተረፋችሁ!” ማለት የፈለጉ ሁሉ፣ በዓሉን እንደየ ስሜትና ፍላጎታቸው አክብረውታል። በዓልነቱ ሽቀላና ገቢ የሆናቸውም አሉ። የግድያና የአፈናውን ዘመን የሚቃወሙትንም “እንኳን ብግን ቅጥል አደረጋችሁ” ለማለት ብቻም የተገኙም ነበሩ። ኢህአዴግ ቅንጅትን ሲከስ […]

ሁላችንም እንደሌላለው ሀበሻ አይደለንም!

ስዎችን የሚለያየን ነገር እንደበዛው ሁሉ፣ የሚያመሳስለንም አንድ እምነት አለ። ይኸውም ሁላችንም “እኛ እንደ ሌላው አይደለንም” ማለታችን ነው። የእኛ እምነት ከሌላው የተሻለ ነው። እኛ ሀበሾች እንደሌላው ዘር አይደለንም። ሌላው ቀርቶ እኛ ሀበሾች እንደሌሎቹ ሀበሾች አይደለንም። እኔ እንደሌላው ወንድ አይደለሁም። ይገርምሃል እኔ እንደሌሎቹ ሴቶች አይደለሁም። ይህ “እኔና እኛ” ፣ “እንደሌላው አይደለንም” የማለት አባዜ፣ በሁሉም ነገራችን ያለ ልበ […]

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios