ጠንካራ አባል መሪ አጥቶ አያውቅም!

ኃይሉ ቅንጅት፣ ብርሃኑ ቅንጅት፣ መስፍን ቅንጅት፣ ልደቱ ቅንጅት፣ ብርቱካን ቅንጅት ይባሉ እንዳልነበሩ ሁሉ ዛሬ ሁሉም የቻሉትን ደጋፊ ይዘው በየአቅጣጫው እየሮጡ ነው። ይሄ ማነው አየለ ጫሚሶ የሚባለው ሰውዬ እንኳ “ቅንጅት ነኝ” ብሎ ከቅንጅት ሊቀመንበር ኃይሉ ሻውል ጋር ለፊርማና ለድርድር አብሮ ተቀምጧል። አቶ ኃይሉ ሻውልም “አንተ ደግሞ የመቸው ቅንጅት ነህ?” ብለው ተገርመው አልጠየቁትም። እንዲያውም ከአቶ መለስ ፓርቲ […]

እኛን የመሰለ መንግሥት?

Today’s Headline – የእለቱ ፍሬ ነገር

እኛን የመሰለ መንግሥት?

እኛን የመሰለ መንግሥት?

ኢትዮጵያውያን ባንድ ነገር እንስማማለን – ብዙዎቻችን አደጋ ይታየናል። አደጋው የሚመጣው ከራሳችን ነው። ራሳችንን እየፈራን ነው። ብንሸነፍ በራሳችን፣ ብናሸንፍ ራሳችንን ነው። ገዢም ተገዢም እኛው ነን። ትግላችን ከራሳችን ነጻ ለመውጣት ነው። የአንድነት ጠላቶች የምናላቸውን ጨምረን አንድ ህዝብ ነን ብለን እናስባለን። ጠላትነትና ወንድማማችነት ተዛዝሎብናል። ከሰዎች ጋር ብቻ ሳይሆን ከገዛ ሀሳቦቻችን ጋር ፀብ ዝምድና አለብን። ከዚህ መታረቅና ማስታረቅ ያለብን […]

ከመንጋው ፈቀቅ በል!

ጊዜው አጭር ነው። አምባገነኖች አይሻሻሉም፣ ጠማሞች አይሰተካከሉም። ደናቁርት አይጠበቡም። ስግብግቦች አይጠግቡም፣ ሌቦች አይታቀቡም፣ ፖለቲከኞቻችን አንድ አይሆኑም..ነጻ ወጪዎቹ ጎሰኞች ነጻ ወጥተው አያበቁም! ተገዢም ሆነው ገዢም ሆነው አየናቸው። የበታችነትና የጥላቻ ስሜትን ከደማቸው ውስጥ ለማጠብ የህይወት ዘመናችን አይበቃም። በዚያ ላይ በዚህች አጭር እድሜ በአጭሩ የሚቀጭ ችግር የለንም። ለውጥ ገና ናት። ተወደደም ተጠላም እውነቱ ይህን ይመስላል። ተስፋ ለማድረግ ተስፋ […]

አባማቶጵያ!

ኦባማ ከምንም ነገር በፊት አንደበታቸው ይጣፍጣል። ስለሆነም በወጣቱ ብቻ ሳይሆን በሁሉ ሰው ጆሮ ፖለቲካን በቀላሉ ሊያንቆረቁሩ ችለዋል። ንግግራቸው እንደኛ አገር የቸከ የመነቸከ ከዓመት ዓመት የማይለወጥ አይደለም። የኛ ንግግር አብዮት- ጎሳ -ብሄር ብሄረሰብ- ነፍጠኞች- ፀረ ህዝቦች… በሚሉት ገፍታሪ ቃላት የተሞላ ይመስላል። እውነት ነው አሜሪካና ኢትዮጵያ ይለያያሉ። አሜሪካውያን ያን ያህል የሰነበተ ሥር የሰደደ ችግር የላቸውም። ከተቸገሩበት የታደሉት […]

አገር በቃላት እየተጫወተ ይመስላል!

አገር በቃላት እየተጫወተ ይመስላል። ለፍትህ ለነጻት ለዴሞክራሲ ለአንድነት ለሰላም ለብልጽግና ለፍቅር….ሁሉም ከእነዚህ ቃላት ጋር ይተኛል። ቃላቱም ከአንዱም ሰው ጋር አይጸኑምና ከሁሉም ጋር ይጎለምታሉ። መጽሐፉ እንደሚል ደግሞ ከጋለሞታ አፍ ማር ይንጠባጠባል። አቤት ሰዎቻችን ሲናገሩ ፖለቲከኞቻችን ሲደስኩሩ መምህራን ሲያስተምሩ እንዴት ደስ ይላሉ። የእግዚሐብሔርን ቃልና ፍቅርን የታደሉት ካህናትማ ስብከትን ሲሰብኩ መስማት ነው። እግዜር ግን ቃል ያጣ ይመስል ስብከትን […]

የአይቲንክ- አይቲንክ ጨዋታ

ኢትዮጵያዊያን ዳር ሆነነ ምራቃችንን በምንውጥለት የሰው አገር ዴሞክራሲ አንዳንዴ ተሳታፊ መሆን ሲያምረን፣ ጥልቅ እንልበትና “የአይቲንክ- አይቲንክ” ጨዋታ እንጫወታለን። “ አይቲንክ አሜሪካ ለጥቁር ፕሬዚዳንት ሬዲ አይደለችም… ። አይሚን ነጮቹ ዘረኞች ስለሆኑ ኦባማን አይመርጡም ። እኔ ግን አይዶንቲክ የአሜሪካ ህዝብ እንደሱ የሚያስብ አይመስለኝም። ምክንያቱም ለውጥ ይፈልጋል። አሁን ግን ይሄ የጥቁርና ነጭ ጨዋታ እየቀረ የመጣ ይመሰለኛል። ዌል፣ አይቲንክ […]

ብሄረ ሰው!

አንድ የሃይማኖት ሰባኪ ምዕመናኑን ሲያሰናብት “በሚቀጥለው እሁድ ውሸት ኃጢአት መሆኑን የሚያብራራ ትምህርት እሰጣችኋለሁ። ለትምህርቴ እንዲረዳችሁ እባካችሁ የማርቆስ ወንጌልን ምዕራፍ 17ን አንብባችሁ ኑ” ይላቸዋል። በሳምንቱ መልካም ምእመናን እንግዲህ ትምህራትችንን ከመጀመራችን በፊት “ስንቶቻችሁ ናችሁ ምዕራፍ17ን ያነበባችሁ?” ብሎ ሲጠይቅ ከጥቂቶች በስተቀር ሁሉም አንብበናል ለማለት እጃቸውን አወጡ። ሰባኪውም “የማርቆስ ወንጌል ከ16 በላይ ምዕራፍ የለውም። ውድ ምዕመናን፣ ውሸት ኃጢአት መሆኑን […]

ህዝብ አላህ!

ሂዝቦላህ ማለት- “ህዝብ አላህ!” ማለት ነው- እኛ የአላህ ህዝብ ነን እንደማለት ነው ብሎ ትንታኔ የሰጠ ሰው መኖሩ ተሰምቷል። በፖለቲካ ጨዋታ መካከል ትንታኔ መስጠት የእያንዳንዱ ስው የንግግር መብት ነውና ዝምብሎ መስማት ዴሞክራሲያዊ ግዴታ ነው። ሂዝቦላን በውስጡ አዝሎ የኔ ነው ወይንም አይደለም ማለት አቅቶት ግራ የተጋባው የሊባኖስ ህዝብም ከኑግ እንደተገኘ ሰሊጥ አብሮ ሲወቀጥ ዓለም እያየ ነው። ሊባኖስ […]

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios