የቤተመንግሥቱ ጄነራል- ፍሬሰንበት

ብርጋዲየር ጄነራል ፍሬሰንበት አምዴ የአሁኑን ጨምሮ በቀደሙት ሁለት መንግሥታ የብሔራዊ ቤተመንግሥቱ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ሠርተዋል። ሶስቱም መንግሥታት ከቤተመንግሥት ያላስወጧቸው ሰው ነበሩ።ንጉሡም ኮ/ል መንግሥቱም አቶ መለስ ዜናዊም ብርጌዲየር ጄነራል ፍሬሰንበትን ከቤተመንግሥት እንዲለዩ አልፈቀዱም። ፍሬሰንበትን ከቤተመንግሥቱ የለያቸው ሞት ብቻ ነው። አሁን በቅርቡ ጥቅምት 16/2001 አርፈዋል። ከ30 ዓመታት በላይ ቤተመንግሥት የኖረ እንዲህ ያለ ባለሟል መችም የሚያወራውም ሆነ የሚወራለት […]

ቅብጠት ወይስ ምን አለበት? የ700 ብር አበባ ለቫለንታይንስ በአዲስ አበባ

አበባ እና ኢትዮጵያ! በኢትዮጵያ በተለይም አዲስ አበባ ኑሮ ተወዷል። ሁሉ ነገር ጨምሯል። ፍቅርም ሳይቀር ጨመረ መሰል የ700 ብር እቅፍ አበባ ይዞ ወደ ፍቅረኞች መሄድ እየተለመደ መሆኑ ተዘግቧል። በተለይ ባለፈው ዓመት የቫለንታይንስ ቀን የአበቦች ዋጋ ሰማይ ነኩና እስከ 700 ብር ድረስ ለመሸጥ በቁ። አባዛኛውን ተራ ህዝብ ያስተናግዳል በሚባለው ገበያ ደግሞ የደከመችና የጠወለገች አንዲት ዘለላ ጽጌሬዳ 10 […]

ከመንጋው ፈቀቅ በል!

ጊዜው አጭር ነው። አምባገነኖች አይሻሻሉም፣ ጠማሞች አይሰተካከሉም። ደናቁርት አይጠበቡም። ስግብግቦች አይጠግቡም፣ ሌቦች አይታቀቡም፣ ፖለቲከኞቻችን አንድ አይሆኑም..ነጻ ወጪዎቹ ጎሰኞች ነጻ ወጥተው አያበቁም! ተገዢም ሆነው ገዢም ሆነው አየናቸው። የበታችነትና የጥላቻ ስሜትን ከደማቸው ውስጥ ለማጠብ የህይወት ዘመናችን አይበቃም። በዚያ ላይ በዚህች አጭር እድሜ በአጭሩ የሚቀጭ ችግር የለንም። ለውጥ ገና ናት። ተወደደም ተጠላም እውነቱ ይህን ይመስላል። ተስፋ ለማድረግ ተስፋ […]

አገር በቃላት እየተጫወተ ይመስላል!

አገር በቃላት እየተጫወተ ይመስላል። ለፍትህ ለነጻት ለዴሞክራሲ ለአንድነት ለሰላም ለብልጽግና ለፍቅር….ሁሉም ከእነዚህ ቃላት ጋር ይተኛል። ቃላቱም ከአንዱም ሰው ጋር አይጸኑምና ከሁሉም ጋር ይጎለምታሉ። መጽሐፉ እንደሚል ደግሞ ከጋለሞታ አፍ ማር ይንጠባጠባል። አቤት ሰዎቻችን ሲናገሩ ፖለቲከኞቻችን ሲደስኩሩ መምህራን ሲያስተምሩ እንዴት ደስ ይላሉ። የእግዚሐብሔርን ቃልና ፍቅርን የታደሉት ካህናትማ ስብከትን ሲሰብኩ መስማት ነው። እግዜር ግን ቃል ያጣ ይመስል ስብከትን […]

Photo Gallery

Designed by Nebxstudios